ከሊስትሮ ወደ አንጋፍ ቡና ኤክስፖርተር - With Asefa Dukamo - S06 EP 59

MERI PODCAST

14-09-2023 • 1 hr 39 mins

እንዴት ቆያችሁን: የተወደዳችሁ የመሪ ፓድካስት ተከታታዮች ። እንኳን በሰላም ወደ አዲሱ አመት ተሸጋገራችሁ ። አመቱ ብዙ ፍሬ ምታፈሩበት : ውጥናችሁ እና እቅዳችሁ ሚሰምርበት አመት እንዲሆን እየተመኘን: ዛሬ ለረጅም ግዜ ስንጠብቀው ከነበረ ልዩ እንግዳ ጋር ቀርበንላችኋል ። በንሳ በምትባል አነስተኛ የገጠር ከተማ ተወልዶ ያደገው የዛሬ እንግዳችን። ከ 13 አመቱ ጀምሮ በንግድ አለም ውስጥ የቆይና : ልምድ ፈትና አጥርታ ያሳለፈችው : በህይወት ከጫማ ማፅዳት ሊስትሮነት ተነስቶ : ስሙ በመላው አለም የቡና ማሸጊያዎች ላይ እስኪሰፈርና : በአከባቢው እንዲሁም በደንበኞቹ ዘንድ በታማኝነቱ ትልቅ ተቀባይነት ማግኘት የቻለ የቡና ኤክስፓርተርነት መድረስ የቻለ :ነው ። አቶ አሰፋ ዱካሞ (አባት) ከአቅራቢያችን ከነአን አሰፋ(ልጅ) ጋር በነበራቸው ቆይታ : ፅናት : ትኩረት : ራስን ዝቅ ማድረግ : ትጋት: ታማኝነት : በአለም መድረክ ላይ መሪ ከሚባሉ እንደነ ስታርባክስ እና ስሌይ የመሳሰሉ የቡና ድርጅቶች ጋር በአጋርነት እስከ መስራት የሚያደርሱ ስንቆች መሆናቸውን የተማርንበት ድንቅ ቆይታ አድርገዋል። ይህን በኛ ዘንድ ትልቅ ቦታ ያለውን የመሪ ክፍል ስንጋብዛችሁ ለአዲሱ አመት መነሻ ስንቅ : ለናንተም ትልቅ የዋጋ ምንጭ እንደሚሆን በማመን ነው ። ለቻናላችን አዲስ ከሆናችሁ ሰብስክራይብ በማድረግ ብዙዎች ጋር መድረስ እንችል ዘንድ አግዙን ! መልካም ቆይታ እየተመኘን በድጋሚ መልካም አዲስ አመት!